About DSKM
የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ክፍል
የስብከተ ወንጌል ትርጉምና ዓላማ
ስብከት ማለት «ሰበከ፤ አስተማረ፤ አግባባ»ከሚለው የግእዝቃል የመጣ ሲሆን፣በጌታ የታዘዘ፣የእግዚአብሔርን ቃል መናገር ፣ወንጌልን ለዓለም መስበክ፣ያላመኑትን ለማሳመን መናገር፣የክርስቶስ ምስክር መሆን ማለት ነው።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ የምሥራች፣ብርሃን፣ የጽድቅ መንገድ፣የነፍስ መስታወት፣የሕይወት ዛፍ የሆነችውን ወንጌልን አስተማረን። ሐዋርያትንም «ሑሩ ውሰተ ኩ(?)ሉ ዓለም ወስብኩ ወንጌለ ለኩ??ሉ ፍጥረት፤ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ»ብሎ እስከ ዓለም ዳርቻ እንዲያስተምሩ ላካቸው።ማር፲፮፥፲፭ ስለኾነም ወንጌል ወደ እግዚአብሔር የሚሔዱባት የምሥራች፤ የብርሃን መንገድ፤ የነፍስ ስንቅ፤ የሐዲስ ኪዳን ተስፋ ማለት ነው፤ጌታችን ሐዋርያትን መስታወት የሆነችውን ወንጌል ይሰብኩ ዘንድ ሲልካቸው የሐዋርያት የስብከታቸው ዓላማ ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለም መግለጥ፣ ምስክር መሆን፣አዳኝነቱን፤ ከሃሊነቱን እና ቤዛነቱን መናገር ነበር፡፡ በሐዋርያት እግር የተተኩት ሐዋርያውያን አበውም ወንጌልን በመስበክ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በመመስከር፣ መድኀኒት ክርስቶስን በመስበክ፣ ሰውነታቸውን ለእሳት አንገታቸውን ለስለት እግራቸውን ለጠጠር ደረታቸውን ለጦር እየሰጡ ምስክርነታቸውን ፈጽመዋል አምላካዊ አደራቸው ተወጥተዋል። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የአበውን ፈለግ ተከትለው ትምህርተ ወንጌልን አምልተው አስፍተው አመሥጥረው ከዘመናችን አድርሰዋል። እኛም ከጌታችን ኋላም ከሐዋርያት እናከሊቃውንት ሲሰናሰል የመጣውን ትምህርተ ወንጌል ሳይከለስ ሳይበረዝ ለተተኪው ትውልድ ለማድረስ ኃላፊነትን ተቀብለናል።
፩**.ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግለጥ፦**
ክርስቶስ «ሥጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወት የለውም» ብሎ በሚያስተምርበት ጊዜ አይሁድ እንዴት የሰው ሥጋ እንበላለን ብለው ይከተሉት የነበሩ በሙሉ ወደ ኋላ ሲመለሱ ሐዋርያትን እንዲህ አላቸው፤«እናንተ ደግሞ ልትሔዱ ትወዳላችሁን?»ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ«ጌታ ሆይ ወደማን እንሔዳለን?አንተ የዘለዓለም የሕይወት ቃል አለህ።እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም» በማለት የዘለዓለም ሕይወት የሆነውን አምላክ መከተል እንዲገባ መስክሯል።ዮሐ፮፥፴ ቅዱስ ያሬድ «ወሪድየ ብሔረ ሮሜ ርኢይክዋ አእመርክዋ ወአፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን፤ ወደ ሮሜ ሀገር ወረድኩኝ ቤተ ከርስቲያንን አየኋት አወቅኋት፤ ወደድኳትም» በማለት ዕውቀት ቀርቦ በማየትና በመውደድ እንደሆነ ይናገራል።ክርስቶስን ማወቅ ማለትም ሃይማኖትን ማወቅ ማለት ነው፤ «ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖትየ ወንጌል» እንዲል (መልክአ ኢየሱስ) ስለዚህ የስብከት ዋናው ዓለማ ሃይማኖትን መስበክ ማሳወቅ በሃይማኖት በጸጋ መንፈስቅዱስ ወደ እግዚአብሔር የሚደረገውን ጉዞ ማሳየትና ሰማያዊ አቅጣጫ መስጠት ነው፡፡
Educating the Young, Guiding the Community
ቅዱስ ጳውሎስ«ተመሰሉ ኪያየ በከመ አነ እትሜሰሎ ለክርስቶስ፤እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ» በማለት፩ኛ ቆሮ ፲፩ ፥ ፩ክርስቶስን እንድንመስለው ይነግረናል።ስብከት ስንል በትሕትና፤ በትግዕሥት፤ በመከራና ክርስቶስን በመምሰል የሚገለጥ ሕይወት ይኖረን ዘንድ የምንማርበት ነው። ሃይማኖታችን የምናጸናበት ምግባራችንን የምናቀናበት መለኮታዊ ጸጋ ነው። ምክንያቱም ምግባራችን የቀና ሃይማኖታችን የጸና ካልሆነ ክርስቶስን መምሰል አንችልምና።ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ «ሃይማኖት ዘእንበለ ምግባር ምውት ይእቲ። ሃይማኖት ያለምግባር የሞተ ነው» ብሎ እንዳሳሰበን ሃይማኖትና ምግባር አስተባብረን መያዝ ይገባል፤ ለዚህ ልዩ ጸጋ ለመታደል ደግሞ ስብከተ ወንጌል የግድ ያስፈልጋል።
እግዚአብሔር ያከበራቸው የመረጣቸው እነርሱም መርጠውት ከዘመድ ባዳ ከሀገር ምድረ በዳይሻላል ብለው ዳዋ ጥሰው ጤዛ ልሰው ደንጋይ ተንተርሰው ድምፀ አራዊቱ ግርማ ሌሊቱ ፀብአ አጋንንቱ ሳያስፈራቸው ስሙን ብቻ ይዘው የወጡትን እናመሰግናቸው እናከብራቸዋለን።ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ«የኑሯቸውን ፍሬ እየተመለከታችሁ ዋኖቻችሁን ምሰሉ»ያለው።በሕጉና በትእዛዙ ጸንተው በጾም በጸሎት ተወስነው ዓለምን ድል ያደረጉ በተጋድሎ ላይ ያሉትም ሕያው ወንጌል ተንቀሳቃሽ እና ሕያው ወንጌል ማለት ናቸውና። በወንጌል ላይ የተጻፈውን የሚተረጉሙ፣ አይቻልም የምንለውን ችለው፣ በተግባር ያሳዩን ናቸው።ጌታችን በወንጌሉ «እውነት እውነትእላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል» በማለትተናግሯል፡፡ዮሐ፲፬፥፲፪ እርሱ እንደተሰደደ ተሰደው፣እንደተራበ ተርበው፣እንደተገረፈ ተገርፈው እንደተሰቀለ ተሰቅለው የክርስቶስን ሕይወት በተግባር የተረጎሙ፤ድውይ እንደፈወሰ ፈውሰው ሙት እንዳስነሣ አስነሥተው በተአምራቱ የተሳተፉ፤ በቅድስና በንጽሕና የሚኖሩትን ቅዱሳንን እናውቅ ዘንድ እንዲሁም አሠረ ፍኖታቸውን እንከተል ዘንድ ስብከተ ወንጌል ያስፈልጋል።
በነቢዩ በኢሳይያስ ላይ አድሮ«ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሣራ ተመልከቱ» እንዳለን ፶፩ ፥ ፪ ቅዱሳን ወንጌልን የምንረዳባቸው የምናውቅባቸው እግዚአብሔርን የምናይባቸው መነጽር ማለት ናቸው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በርካታ መምህራንም እያስተማረች በየቦታው ስታሰማራ ኖራለች፤ ወደፊትም ይህንን ተልእኮዋን ትቀጥላለች፤ ምክንያቱም ስብከተ ወንጌል ቃለ እግዚአብሔርን ለማስተማር ብቻ ሳይኾን የሰውን አእምሮ ለማልማት እና መልካም አስተሳሰብን ለመገንባት የሚያስችል ዋነኛው የቤተክርስቲያን መሣሪያ ነውና፡፡
Our Purpose: Spreading the Gospel
Our Purpose: Spreading the Gospel, Administering Sacraments, and Providing Spiritual and Social Services to the Community in Washington D.C. Our church, re’ese adbarat debre selam kidist mariam, was founded in 1987 to fulfill these noble objectives. With over 1500 registered members, we are the largest Ethiopian Orthodox parish in the Washington metropolitan area. Our vibrant community is dedicated to upholding the faith, teachings, and traditions of the mother church in Ethiopia.
Faith, Worship, and Community Together
Through our spiritually inspired initiatives, we have been faithfully fulfilling our mission for the past thirty-three years, playing a vital role in baptizing infants, administering the sacrament of holy matrimony, and conducting memorial services for the repose of the dead in our community. We hold regular worship services, morning and evening prayer services, and live stream many of these services for the benefit of members unable to leave their homes. Our dedicated council of clergymen and over a hundred members organized into more than ten committees provide crucial help in successfully executing our church’s objectives and annual proposals.